FULLNESS OF CHRIST CHURCH (FCC)
IN MINNESOTA

የክርስቶስ ሙላት ቤተ ክርስቲያን በሚኒሶታ
“እርሷም ሁሉን ነገር በሁሉም ረገድ የሚሞላ የእርሱ ሙላቱ የሆነች አካሉ ናት።”  ኤፌ 1፡23
አድራሻችን (Our Address): 700 Diffley Rd, Eagan, MN 55123
Serving Ethiopian and Eritrean communities.

የክርስቶስ ሙላት ቤተክርስቲያን መሰረተ እምነት

ስላሴ

ሁሉን በሚችል ፍፁም በሆነ ሰማይና ምድርን እንዲሁም በውስጧ ያሉትን ሁሉ በፈጠረና በሚገዛ ለዘላለም በአንድነትና በሶስትነት በሚኖር በእግዚአብሔር አብ፤በእግዚአብሔር ወልድ እና በእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ /ስላሴ/ እናምናለን፡፡ማቴ 28፡-19 ዮሀ 17፡-3 ቆሮ13፡-14 በእግዚአብሄር አብ ወልድና መንፈስቅዱስ በመፍጠር፤ ፍጥረትን በመጠበቅና ፍጥረትን በማስተዳደር በመዋጀት ፍፁም ስልጣንና ሉዓላዊነት እናምናለን፡፡ ሮሜ 9፡15-16 ኤፌ 1፡11


መጽሀፍ ቅዱስ

ስልሳ ስድስቱን የብሉይና የአዲስ ኪዳን መፃህፍትን የያዘው መፅሀፍ ቅዱስ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ሰዎችን ተጠቅሞ የተፃፈ ምንም ስህተት የሌለበት እግዚአብሔር እራሱንለሰው ልጆች ደህንነት የገለፀበት የማይጨመርበት፤ የማይቀነስበት ብቸኛና የመጨረሻ ስልጣን ያለው በፅሁፍ የቀረበ እስትንፋሰ መለኮት ያለበት የእግዚአብሔር ቃል እንደሆነና ለአማኞች እምነትና ኑሮ አዛዥ ፤መሪና ባለሙሉ ስልጣን መሆኑን እናምናለን፡፡2ጢሞ 3፤16-17 2ጴጥ 1፤19-21


ኢየሱስ ክርስቶስ

ከዘላለም የአብ የባህሪ ልጅ መሆኑን፤ ከአብ የተላከ መሆኑን፤ ፍፁም አምላክ መሆኑን፤ ከመንፈስ ቅዱስ ተፀንሶ ከድንግል ማርያም የተወለደ፤ ለሰው ልጆች ሁሉ ሀጢያት ሲል በመስቀል ላይ ተሰቅሎ እንደሞተ፤እንደተቀበረ ወደ ሲኦል እንደወረደ፤በሶስተኛውም ቀን በስጋ ከሞት እንደተነሳ ወደ ሰማይ እንዳረገ፤ አሁን ሊቀካህናችንና ጠበቃችን ሆኖ በአባቱ ቀኝ እንዳለ፤ተመልሶ በክብርና በግርማ እንደሚመጣ እንደሚፈርድም እናምናለን፡፡ ማቴ 1፡23 ዮሀ1፡1 ሐዋ 1፡11 ዕብ 9፡24


መንፈስ ቅዱስ

ፍፁም አምላክ እንደሆነና ክርስቶስን እንደሚያከብር ሰዎችን ስለ ሀጢያት በመውቀስ ዳግም እንዲወለዱ እንደሚያደርግ፤ በአማኞች ውስጥ እንደሚኖር እውነትን እንደሚያስተምርና እንደሚመራ፤ ለተቀደሰም ኑሮና አገልግሎት በሀይሉ እንደሚያስታጥቅ፤ በስጦታዎቹም እንደሚሞላ፤ ህልውና ያለው አካላዊ መንፈስ አንደሆነ መንፈስ ቅዱስ ለአማኞች ልዩ ልዩ የፀጋ ስጦታዎችን በማካፈል፤ ድውዮችን በመፈወስ፤ አጋንንትንበማስወጣትና ተዓምራትን በማድረግ ዛሬም ህያው ሆኖ እንደሚሰራ እናምናለን፡ ዮሀ 4:24 ማቴ 28:19-29ዮሀ 14:26ሀዋ 2:38ሀዋ 13:41ቆሮ12:7


ሰው

በእግዚአብሔር አምሳል መፈጠሩን፤ በሀጢያት የወደቀና የጠፋ በዚህም ምክኒያት የእግዚአብሔር ቁጣና ፍርድ ያለበት በደለኛ መሆኑን እናምናለን፤ በገዛ ስራው ሳይሆን በመንፈስ ቅዱስ እርዳታ የጌታ ኢየሱስን የመስቀል ላይ ስራ አምኖ በእምነት በመቀበል ዳግም ልደትንና ድነትን እንዲሁም ህያው የሆነ መንፈሳዊ ህይወትን እንደሚያገኝና በኢየሱስ ክርስቶስ አምኖ ዳግመኛ በመወለድ አዲስ ፍጥረት በመሆን መንፈስ ቅዱስ በሕይወቱ እንደሚሰራ እናምናለን፡፡ ዮሀ 1፡2 2ቆሮ 5፡21 ሐዋ 4፡12 ሮሜ 3፡23 ሮሜ 5፡ 12 ቲቶ 3፡5-7


ቅዱሳን መላእክት

በእግዚአብሄር የተፈጠሩ መንፈሳዊ አካል የለበሱ እና በእግዚአብሔር ፈቃድ የሚያገለግሉ በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠረውን ሰው በተለይም አማኞችን ከእግዚአብሔር ተልከው እንደሚረዱ እናምናለን፡እብ 1:7ዳን 10:13 ራእይ 1:1 ራእይ 9:10


ሰይጣን

በእግዚአብሔር ላይ አምጾ ሌሎችን መላእክት አሳምጾ ከእግዚአብሔር ክብር ፊት የተጣለ የሀሰት ሁሉ አባት፤የሀጢያት ሁሉ ምንጭ እንደሆነና አብረውት የወደቁት ርኩሳን መናፍስትም ስራቸው ዘወትር ክፉ እንደሆነና በተጨማሪም የእግዚአብሔርና የሰው ልጆችም ሁሉ ጠላቶች እንደሆኑ እናምናለን፡፡ ኢሳ 14 ራእይ 12፡7-9


ቤተክርስቲያን

መሰረቷና ራሷ ክርስቶስ በሆነ በጌታ በኢየሱስ የመቤዠት ስራ አምነው ድህነትን ተቀበሉ ሁሉ የሚገኙባት የክርስቶስ አካልና ሁሉን በሁሉ የሚሞላ የእርሱ ሙላቱ በሆነች አንዲት አለም አቀፍ ቤተክርስቲያን እናምናለን፡፡ የዚህችም የማትታየዋ ቤተክርስቲያን አባላት የሆኑቱ ብቻ የአጥቢያ ቤተክርስቲያን አባላት መሆን እንደሚገባቸውና እናምናለን፡፡ኤፌ 1፡22&23 ኤፌ 4፡4 ቆላ 1፡10


የውሃ ጥምቀት ስርዓት

አማኞች በውሀ ውስጥ በመጥለቅ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ባዘዘው መሰረት ከክርስቶስ ሞትና ትንሳኤ ጋር መተባበራቸውን ለመግለፅና ለመመስከር የሚያደርጉት መንፈሳዊ ስርአት ሲሆን ከኢየሱስ ጋር መሞታቸውን በውሀ ውስጥ በመቀበር ከእርሱም ጋር በአዲስ ህይወት መነሳታቸውን ከውሀውስጥ በመውጣት ሲመሰክሩ የጥምቀቱም ስርዓት የሚፈፀመው በአብ፤ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ አንድ አምላክ ስም መሆኑና እናምናለን፡፡ ማቴ28፡18-19


የጌታ እራት

የጌታችን የመድሀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ስቃይና ሞት እንድናስብ የሚያሳስበን በአማኞች መካከል መደረግ ያለበት የተቀደሰ ስርዓት እንደሆነና ይህን ስራት ስንፈጽም የጊታን ሞትና ትንሳአኤ አንደምንናገር ይህም ስርአት ራስን በመመርመርና በቅድስና ገብቶንና ተረድተነው ልንፈጽም አንደሚገባን እናምናለን፡፡ 1ቆሮ 11፡23


ክርስቲያናዊ ጋብቻ

በአንድ አቅመ አዳም በደረሰ አማኝ ወንድ እና በአንዲት ለአቅመ ሄዋን በደረሰች አማኝ ሴት መካከል የሚፈፀም የእድሜ ልክ ኪዳን እንደሆነ እናምናለን፡ጋብቻ በወንድና በሴት ጾታ መካከል ብቻ እንደሚደረግና አንድ ወንድ ለአንድ ሴት ብቻ ተወስኖ የሚኖርበት ቃልኪዳንና እንደሆነና በክቡር ጋብቻ መካከል ጋብቻን ማክበርና መንከባከብ እንደሚገባቸው እናምናለን፡፡ ዘፍ 2:24 ሚል2 ኤፌ5:25


አስራትና መባ

አስራትና መባ እንዲሁም ስጦታዎችን በመስጠት ቤተክርስቲያንን ማገልገል እንዲሁም ድሆችን፤ መበልቶችን፤አካለ ጎዶሎዎችን ሴተኛ አዳሪዎችን፤ የጎዳና ተዳዳሪዎችን እንዲሁም ወላጅ የሌላቸው ህፃናትን መርዳትና መንከባከብ አስፈላጊ እንደሆነ እናምናለን፡፡ 2ቆሮ 9:10-111ቆሮ 9፡13-14 1 ጢሞ 6:18-19


የአማኞች ሞት

የአማኞች ሞት ማንቀላፋት አንደሆነ እናምናለን፡ጌታ እስኪመጣ ድረስ ህያው ሆነው የሚቀሩት ካለሆኑ በቀር ጌታ አንዳንዶቹን በራሱ ፈቃድ እንዲያንቀላፉ(እንዲሞቱ) እንደሚያደርግ እናምናለን፡፡ 1ተሰ4፡15 የሞቱ ሁሉ በስጋ ትንሳኤ ከሞት እንደሚነሱ የሚበሰብሰው አካል የማይበሰብስ ሆኖ እንደሚነሳና አማኞች ከጌታ ጋር ወደ ዘላለም በረከትና ደስታ በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የማዳን ስራ የማያምኑት ዳግም ወደ ዘላለም ፍርድ እና ቅጣት እንደሚሄዱ እናምናለን፡፡ ራዕይ 20 ዮሀ 5፡28-29 1ቆሮ15


ዳግም ምጻት

ጌታ ዳግም ሲመጣ መንግስቱን በምድር ላይ እንደሚተክልና ሺህ አመት እንደሚገዛ የፊተኛውን ትንሳኤ ያገኙ ቅዱሳንም ከእርሱ ጋር በመሆን በሺህ አመቱ አገዛዝ እንደሚነህሱ እናምናለን፡፡ ራዕይ 20፡1-6


የአማኞች ቅድስና

አማኞች ከአለማዊነትና በአለም ከሚገኙት ከንቱ የስጋ ፍሬዎች ተለይተው ለቅድስና ኑሮ እንደተጠሩ እናምናለን፡፡ ሮሜ 12፡1-2 2ቆሮ 6፡14 ቲቶ 2፡11-14 1ኛ ዮሀ 2፡15-17